Senior Electrician

Apply Now
  • location
    Location Type : Office
  • calendeer
    Deadline : December 18th, 2026
  • career
    Career Level : Senior(5-8 years)
  • employment_type
    Employment Type : Full time
  • career
    Number of people required : 1
  • career
    Work Experience : 5-8 years
View all open positions
About the Job

  • የዕለቱ በሚከናወኑ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ምርመራ ጊዜ ችግሩን ምንጭ በማውጣት ከነመፍትሔው በዝርዝር ለቅርብ ኃላፊው ሪፖርት ያቀርባል፤ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ጥገና ያከናውናል፡፡
  • ለጥገና የሚፈልጉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ዝርዝር መግለጫዎችን (Specifications) በማውጣት ለቅርብ ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፡፡
  • ለኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሥራ የሚፈልጉ መሣሪያዎችና የመፈተሻ መሣሪያዎች፣ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ የኤሌክትሪክ ማቀናበሪያ እቃዎችና ማቴሪያዎች ተለይተው እንዲገቡ ይጠይቃል፤ ማሟላቱንም ያረጋግጣል፡፡
  • ድንገተኛና ያልተጠበቁ ብልሽቶችን ወይም በፕሮግራም መሠረት የሚጠበቁ የንክብካቤ ጥገና ሥራዎችን በሚደርሰው የሥራ ግዜ መሠረት ይሠራል፣ ያስተባብራል፤ የመጨረሻ ፍተሻ ያደርጋል፤ በትክክል መፈጸማቸውን ያረጋግጣል፡፡
  • ለመሳሪያው ጥገና የሚደረግ የቴክኒክ ዲዛይን ያወጣል፤ በዚሁ መሠረት የቴክኒክ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡
  • የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሥራውን የፈጀውን የሥራ ሰዓት፣ የተጠቃሚውን እቃና የመሳሰሉ ሁኔታዎችን አሳይቶ ሪፖርት ያደርጋል፡፡
  • አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ማኑዋልና መመዘኛዎች ሲገቡ ይሳተፋል፡፡
  • በማምረቻ መሳሪያዎች ላይ የሚደርሰውን የኤሌክትሮኒክስ ሲስተም፣ የኤሌክትሪክ ክፍሎችና ትራንስፎርመር ክትትል ያደርጋል፡፡
  • በኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሥራ ጊዜ አስፈላጊውን መረጃዎች በማቅረብ በዝግጅቱ ላይ ይሳተፋል፡፡
  • ለዓመቱ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና የሚፈልጉ እቃዎችና መለዋወጫዎች ዝርዝር በማዘጋጀት አቅርቦ ያስፈጽማል፤ በግብግብ በሥራ ላይ ይውላል፡፡
  • ለሥራ ተጠይቆ ከምርት ውጭ ወይም ውጪ ተገዝቶ ከመጣ እቃዎች/መለዋወጫዎች ከተጠየቀው ጋር ተስማሚ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ልዩነት ሲኖር ለቅርብ ኃላፊው በወቅቱ ያሳውቃል፤ እንዲስተካከሉም ያደርጋል፡፡
  • የተበላሹና የተፈቱ እቃዎች እያሰባሰበ ለቅርብ ኃላፊው በማሳወቅ ተገናኝተው በሥራ ላይ ሊውሉ የሚችሉትን በመገንዘብ ለሥራ ዝግጅት ያደርጋል፡፡
  • መሳሪያዎች ሲተከሉ ወይም በተለያየ ምክንያት የይዞታ ለውጥ ሲደረግላቸው የተመደቡትን ዓላማዎች በማስተካከል የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎችን ያከናውናል፡፡
  • በኤሌክትሮኒክስ አጠቃቀምና መምሪያ አጠቃቀም ስላደረሱ አዳዲስ ሁኔታዎች የድርጅቱ ሠራተኞች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡
  • በድርጅቱ ውስጥ ሊገኙ የሚችሉትን ጥገናዎች ውጭ ራንክ እንዲሠሩ ለቅርብ ኃላፊው ሪፖርት እያደረገ ሲፈቀድ ተከታትሎ ይሰራል፤ ተሰርተው ሲወጡም ትክክለኛነቱን ፈጥሮ በመረጋገጥ ይረከባል፡፡
  • የድርጅቱን የሥራ ደህንነት ሕግ ያከብራል፡፡
  • የማምረቻ መሳሪያዎች የጥገናና የንክብካቤ መመሪያን በሥራ ላይ ያውላል፡፡
  • አዲስ ቴክኖሎጂን ሊያስተዋውቁ የሚችሉትንና ፈጠራ ሥራ ሊያዳብሩ የሚችሉትን ሁኔታዎች በመምረጥ ለቅርብ ኃላፊው ሐሳብ ያቀርባል፡፡
  • ሌሎች ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ተዛማጅ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡

About You

መስፈርት፡- በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ወይም በኢንዱስትሪ ኤሌክትሪሲቲ የቴክኒክ ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ፤ በተለይም በ PVC ፋብሪካ ኤክስትሩደር (extruder) ላይ ጠንካራ ዳራ/ልምድ ያለው፤ ስለ PLC እና ኢንቨርተር (Inverter) በቂ እውቀት ያለው፤ እንዲሁም የቅድመ ጥገና እና የችግር ፈቺነት (Preventive maintenance trouble shooting) ክህሎት ያለው።

የሥራ ልምድ፡- በ PVC ፕላስቲክ ፋብሪካ ውስጥ የሰራ 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ።

ጾታ፡- ወንድ።

Requirement Skill
    Electrical Engineering, Automation Engineering,   technical education.
How To Apply

Please submit your updated CV and work experience documents to the email address below:

Perks + Benefits
Medical Allowance

Medical Allowance

Meal

Meal

More Jobs by AZ Pipe Manufacturing
Search Similar Jobs in Senior Electrician
Jobs in Engineering
Jobs for Senior(5-8 years)
Jobs in Addis Ababa