ስለ ኩባንያው
መሠረት ማሬ ሶላር አስመጪ፣ ተከላ እና ገጣሚ በኢትዮጵያ የታዳሽ ኢነርጂ ዘርፍ ግንባር ቀደም ተቋም ሲሆን፣ ጠንካራ እና ራሱን የቻለ የገጠር ማህበረሰብን የመፍጠር ታላቅ ራዕይ ሰንቆ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው። ድርጅታችን በገጠሩ የሀገራችን ክፍሎችና በግብርና ማዕከላት ዙሪያ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ሕይወት ለመለወጥና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ፤ ንጹህ፣ ዘመናዊና አስተማማኝ የሶላር ኃይል አማራጮችን፣ የሶላር የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን (Solar Water Pumps) እንዲሁም ለግብርናና ለተለያዩ የምርት ተግባራት የሚውሉ የሶላር ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ድርጅታችን ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት 2 የስራ መደቦች ብቁ እና ባለሙያ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡
የስራ ቦታዎች፡
1. የቴክኒክና ጥገና ባለሙያ | ||
የስራ ክፍል፡ የቴክኒክ ክፍል | ብዛት፡ ለእያንዳንዱ ቦታ 1 (በአጠቃላይ በ4 የስራ ቦታዎች 4 ክፍት የስራ መደቦች) ዋና ዋና ኃላፊነቶች፡
|
1. የቴክኒክና ጥገና ባለሙያ
ተፈላጊ መስፈርቶች፡ በኤሌክትሪክ/ኤሌክትሮኒክስ፣ ታዳሽ ኢነርጂ፣ የኢንዱስትሪ ተከላ ወይም ተዛማጅ የቴክኒክ መስኮች የቲቪኢቲ (TVET) ሰርተፍኬት (ደረጃ ||| ወይም ከዚያ በላይ) ያለው/ያላት እና ከ2 ዓመት በላይ ተግባራዊ የሶላር ተከላ እና ጥገና ልምድ ያለው/ያላት፡፡
2. የሶላር ማርኬቲንግ ባለሙያ
ተፈላጊ መስፈርቶች፡ በኤሌክትሪካል፣ መካኒካል፣ በታዳሽ ኢነርጂ፣ በማርኬቲንግ ወይም ተዛማጅ መስኮች ዲፕሎማ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ቢያንስ 2 ዓመት የሽያጭ/ማርኬቲንግ ልምድ እና ስለ ሶላር ኢነርጂ ሲስተሞች ጠንካራ ግንዛቤ ያለው/ያላት፡፡
የተለመዱ የስራ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች (ለሁለቱም የስራ መደቦች)
ቋንቋ እና መኖሪያ ቦታ፡ ፕሮጀክቱ የሚገነባበት አካባቢ ነዋሪ እና የአካባቢውን ቋንቋ አቀላጥፎ የሚናገር (ለአካባቢው ነዋሪዎች እና ቋንቋ ተናጋሪዎች ቅድሚያ ይሰጣል)፡፡
ፍላጎት ያላቸው እና መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች ሲቪ (CV)፣ የሚያመለክቱበትን የስራ መደብ፣ የሚፈልጉትን የስራ ቦታ፣ የሚኖሩበትን አካባቢ እንዲሁም የሚናገሩትን ቋንቋ የሚገልጽ ማመልከቻ ደብዳቤ እስከ ህዳር 11፣ 2019 ዓ.ም ድረስ በኢሜል አድራሻችን [email protected] መላክ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡ እባክዎ በማመልከቻዎ ላይ የአሁኑን የመኖሪያ ቦታዎን እና አቀላጥፈው የሚናገሯቸውን የአካባቢ ቋንቋዎች በግልጽ ይጥቀሱ፡፡