መግቢያ
ሚዳ እመርታ (MEDA/EMRTA) ፕሮጀክት (እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ2016-2022 የሚቆይ) በካናዳ መንግስት አለምቀፍ ጉዳች (Global Affairs Canada) ድጋፍ በአማራ ክልል በሩዝ፣ አትክልትንና በከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ምርት እሴት በመጨመር ለተሰማሩ ተቌማት፣ ጥቃቅን፣ አንስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች ገቢያቸው እንዲያድግና የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ እገዛ በማድረግ ላይ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡
ዓላማ
የፕሮጀክቱ ዓላማ አዳዲስ ፈጠራዎችን በማገዝ ሩዝ አትክልትንና የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት በዘመናዊ ዘዴ በማምረት፣ በማቀነባበርና እስከ ተጠቃሚው ድረስ ያለውን ሰንሰለት/ትስስር ደረጃውንና ጥራቱን የጠበቀ ምርት በማማረት በተለይ ሴቶችን ይበልጥ ተጠቃሚ በማድረግንና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚከናወኑ ተግባራትም ከአካባቢ ደሕንነት እንክብካቤ ጋር የተጣጣሙ ፕሮጀክቶችን በመደገፍ የአማራንና ብሎም የኢትዮጵያን እኮኖሚ እንዲያድግ የበኩሉን አስተዋጽዖ ለማበርከት ነው፡፡
በመሆኑም በክልሉ የሚመረቱት ሩዝ አትክልትና የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ዙሪያ ዘመናዊ በሆነ ዘዴ እሴት በመጨመር ለምትንቀሳቀሱ ሁሉ የፕሮጅክት ሃሳባችሁን አዘገጅታችሁ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል፡፡
ሊቀርቡ ከሚችሉ የፕሮጀክት ሃሳቦች መካከል
ሩዝ
· የማቀነባበሪያ መሳሪያ ግዢ (የደረጃ መውጫ፣ የእርጥበት መለኪያ፣ በመስመር ለመዝራትና ለመትከል የሚረዳ መሳሪያ፣ ማድረቂያ፣ የሩዝ መቀቀያ፣ የምርት ማከማቻ፣ ማሸጊያ፣ የምርት ማሰባሰቢያ … ወዘተ
· በሥራ ላይ ያሌ ቴክኖሎጂዎችን ማሳደግ/ማስፋፋት
· የተሻሻለ/ምርጥ የሩዝና አትክለት ዘር ማምረት/ማሰራጨት
· ማቀነባበር (ማሸግ፣ ደረጃ መውጣት፣መሰየም…)
· በግል የተሸሻለ ዘር ማባዛትና ግብይት
· ባዛርና እግዚቢሽን መሳተፍ
· ምርትን ለሽያጭ ማሰተዋወቅ
· የግብይት መረጃዎችን ማሰራጨት
· ምርት በተጠቃሚዎች ዘንድ ለማስተዋወቅ ለሚድረግ
· አድቮኬሲ የተግባቦት ሥራ፣ ለምዝገባ፣የብቃት ማረጋገጫ
አትክልት
· የምግብ/የቲማቲም ድልህ/ ማቀነባበሪያ መሳሪያ ግዢ እና መመስረት
· ቲማቲም እና ሽንኩርት ማድረቂያ ማሽኖችን እና ክህሎቶች ማስተዋወቅ
· በሥራ ላይ ያሌ ቴክኖሎጂዎችን ማሳደግ/ማስፋፋት
· ቀላልና በተመጣጣኝ ዋጋ ሊገኙ የሚችሉ የመስኖ ቴክኖሎጅዎችን ማስተዋወቅና ማስራጨት
· የተሻሻለ/ምርጥ/ዲቀላ የአትክልት/ የሩዝና ዘር ማምረት/ማሰራጨት
· ማቀነባበር (ማሸግ፣ ደረጃ መውጣት፣መሰየም…)
· አካባቢን የማይበክሉና ተፈጥሮዊ የሆኑ ማዳበሪዎችን አና ተባይ እና በሽታዎችን መካላከያዎችን ማስተዋወቅና ማሰራጨት
· ባዛርና እግዚቢሽን ለመሳተፍ
· ምርትን ለሽያጭ ማሰተዋወቅ
· ምርት በተጠቃሚዎች ዘንድ ትውውቅ ለማድረግ
· አድቮኬሲ የተግባቦት ሥራ፣ ለምዝገባ፣የብቃት ማረጋገጫ
· የምርት ማከማቻ፣ ማጓጓዣ፣የምርት ማሰባሰቢያ
የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት
· የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናትን ለመቁረጥና ለማለስለስ (ላፒዳሪ) ሥራ ለማስፋፋትና የማቀነባበሪያ መሳሪያ ግዢ፣
· የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናትን ተጠቅመው ጌጣጌጥ የሚሠሩ የጌጣጌጥ አምራቾች (ጀውለሪይ) ሥራ ለመሥራትና የማቀነባበሪያ መሳሪያ ግዢ፣
· በሥራ ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን/ የጌጣጌጥ ማድናትን የመቁረጥና ማስዋብ እንዲሁም የጌጣጌጥ ማቀነባበሪያ የሚያገለግሉ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ መሳሪያዎችን/ ማሳደግ/ማስፋፋት፣ማምረትና ማቅረብ፣
· የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናትን በመጠቀም ልዩ ልዩ የቤትና የቢሮ ቁሳቁስ እንዲሁም የስጦታ ዕቃዎችን ለማምረትና ለገበያ ለማቅረብ፣
· የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናትን ውጤቶችና ጌጣጌጦች ወደ ውጭ ለመላክ/ኤክስፖርት/ ለማድረግ፣
· በከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ውጤቶች ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ሥራ ልማት አገልግሎት ለመስጠት ፣በሥራ ዘርፉ በሚካሄድ ባዛርና እግዚቢሽን ለመሳተፍ፣
· የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ውጤቶች ምርትን ለሽያጭ ማቅረብና ማሰተዋወቅ፣
· አድቮኬሲ/ የተግባቦት ሥራ፣ ለምዝገባ፣የብቃት ማረጋገጫ
በፕሮጀክቱ የማይሸፈኑ
የፕሮጅክቱን ዓላማ የማያሳኩና ከሩዝ አትክልትና የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ጋር ግንኙነት የሌላቸው ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ድጋፍ አይደረግላቸውም፡፡
· ተጨባጭ ለውጥ እንዴት እንደሚመጣና ዘላቂነቱን በደንብ ያላመላከተ የፕሮጀክት ሃሳብ
· ከእመርታ ፕሮጀክት መጠናቀቅ በኋላ ፕሮጅክቱ በራሱ ድግፍ እንደሚቀጥል ያላስቀመጠ የፕሮጀክት ሃሳብ
· አሰተዳዳረዊ ወጪዎች ለምሳሌ፡- ቌሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ መደበኛ ወጪዎች፣ የሥራ ማስኬጃ ወጪ፣ አሰቀድሞ ለተሰጠ ብድር/ዕዳ መመለሻ/መተኪያ
· ከአካባቢ እንክብካቤ ጥበቃና ከሥርዓተ-ፆታ ጋር ያልተጣጣመ የፕሮጀክት ሃሳብ
· ለአንድ ፕሮጀክት ከ500 በታችና ከ100,000 የካናዳ ዶላር በላይ የያዘ የፕሮጀክት ሃሳብ አይሰተናገድም፡፡
አመልካቹ ማሟላት ያለባቸውና ተፈላጊ ሰነዶች
· የንግድ ፈቃድ
· የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
· እንደ ፕሮጅክት ሃሰቡ ዓይነት የሚወሰን ሆኖ ከ1-2 ዓመት የተሳካ ሽያጭና ትርፍ ስለማስመዘገቡ የሚያረጋግጥ ማስረጃ
· አመልካቹ በክልሉ ውስጥ የሚመረቱትን ምርቶች ላይ ተመስረቶ የተዘጋጀ የፕሮጅክት ሃሳብ ስለመሆኑ (ፕሮጀክቱ በሚተገበርበት አካባቢ ያለው ሕዝብ እንዴት ተጠቃሚ እንደሚደርግ ማመላከት ይኖርበታል)፡፡
· አመልካቹ የፕሮጀክቱን ጠቅላላ ወጪ ቢያንስ ያቀረብውን የፕሮጀክት ወጨ 30% የሚሸፍን
· የፕሮጀክት ሃሳቡ በተለየ መንገድ ሴቶችን እንዴት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ማመላከት ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ግን ወንዶችን አይመለከትም ማለት አይደለም፡፡
· የሚታሰበው ፕሮጀክት ከአካባቢ ጥበቃ እንክብካቤ ጋር የተጣጣመ መሆን ይኖርበታል፡፡
· የፕሮጀክት ሃሳቡ ከታች በተመለከቱት አስቀድሞ በተዘጋጁ ወጥ በሆኑ ቅፆች ተዘጋጅቶ መቅረብ ይገባዋል፡፡
ü የፕሮጀክት ሃሳብ ማቀረቢያ ቅጽ
ü ዝርዝር የተግበራ መርሃግበር ቅጽ
ü የፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የወጪ ግምት